የመስረታ በአሉ አንድ አመት በሚቆይ ዝግጅት የሚከበር መሆኑንም ባንኩ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል ።
ህብረት ባንክ 25 አመት የምስረታ በአሉን ህዳር 13 በሸራተን ሆቴል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሊያከብር መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑን አቶ መላኩ ከበደ አስታውቀዋል።
በዛሬው እለት በህብር ታወር የባንኩን 25 አመት አስመልክቶ የአርማ ምርቃት እና የኢግዚብሽን መርሃ ግብር አከናውኗል።
ህብረት ባንክ በ1991የተመሰረተ ሲሆን አሳታፊ እና ሁሉን አቃፊ የባንክ አገልጎሎት ለመስጠት ያለመ እንደነበር የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው በየአመቱ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ባንሉ በ25 አመታት ጉዞ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለማህበረሰቡ በማድረሱን እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ባንኩ በኢትዮጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ16 አመት በፊት የሞባይል ባንኪንግ እና ኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎት በባንኩ መጀመሩን አስታውሰዋል።
የባንኩን ዋና መስሪያ ቤት ዘመናዊ ባለ 32 ህንጻ ህብር ታወርን በ6 አመታት ውስጥ መገንባታቸውንም ጠቁመዋል።
የህብረት ባንክ የምስረታ በአል አስመልክቶ በአዲስ አበባ እና በመላ የሃገሪቱ ክፍሎች በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተናግረዋል።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ መላኩ ከበደ እንደተናገሩት ያልታሰቡ ያሏቸው በአለም አቀፍ ሆነ በኢትዮጲያ የተከሰተው የኮቪድ ወረርሽ እንዲሁም በሀገሪቱ የተከሰትወው ግጭቶች እንደ ተግዳሮቶች አንስተዋል።
የባንኩ ካፒታል 9.3 ቢሊየን ብር በላይ ሲሆን 475 የሚሆኑ የህብረት ባንክ ቅርንጫፍ መኖሩን ጠቅሰው ከ8ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰራትኞች የስራ እድል መፈጠሩን ተገልጿል።
እሌኒ ግዛቸው
ህዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም