በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተከሰተው ድርቅ በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ተናግረዋል፣ ድርቁን ተከትሎ በተፈጠረ የጤና ቀውስ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርና በሰሜን ጎንደር ዞን 40 የሚጠጉ ሰዎች ህይወት አልፏል ተብሏል፡፡
ሰኔና ግንቦት መጣል የነበረበት ዝናብ ባለመጣሉ በሰሜን አማራ አካባቢዎች በሚገኙ ወረዳዎች ድርቅ መስፋፋቱንና በእንስሳትና በሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ እንደሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
የነዋሪዎች አስተያየት
በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሳህላ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሻምበል ግርማይ ድርቁ ካለው የሰላም መደፍረስ ጋር ተያይዞ ለመኖር ፈተና ሆኗል ይላሉ፣ በቂ እርዳታም እንዳላገኙ ነው የሚገልፁት፡፡አማራ ክልል ሰዎች በድርቅ የተነሳ እየሞቱ ነው
“ተበዳድረን ከባለፀጋ ሸምተንም ሆነ ሸቅለን ብንመጣም ስቃዩ ብዙ ነው፣ አንዳንድ ድርጅቶች እርዳታ መስጠት ቢሞክሩም ከእርዳታው አነስተኛነት የተነሳ የፀብ መነሻ ሆነ” ተፈናቅሎ የሚኬድበት ቦታ እንኳ የለም ምክንቱ ደግሞ የሰላም አለመረጋጋት ሌላ ችግር እንደሆነባቸው ነው የሚናገሩት ህፃናትና እናቶች እታመሙ እየሞቱ እንደሆንም አመልክተዋል፡፡
ወ/ሮ ሙሉ መኮንን በበኩላቸው ድርቁ በፈጠረው ከፍተኛ ተጠዕኖ የወረዳው ህዝብ “ቀኑ ጨልሞበታል” ይላሉ፡፡
“ድርቁ ዘንድሮ ተለየ ነው፣ ህዝቡ ሌቱም ቀኑም ጨልሞበታል፣ ድርቁ አንግግቦናል፣እርዳታውም በቂ አይደለም ነው ያሉት፡፡”
የወረደ ባለስልጣናት አስተያየት
በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳምጠው አባቡ በወረዳው 6 ቀበሌዎች ከ30 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በድርቁ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፣ በተለይም የመጠጥ ውሀ እጥረት ከሁሉም የከፋ ነው ሲሉ ነው ችግሩን የገለፁት፡፡
በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዓለሙ ክፍሌ መንግስት በሚቆጣጠራቸው 6 ቀበሌዎች ድርቅ መከሰቱ አመልክተው 10ሺህ ያህል ነዋሪም ቀየውን ለቅቆ ተፈናቅሏል ነው ያሉት፡፡በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የተከሰተው ድርቅ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ
የዞን ባለስልጣናት ምላሽ
የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ አጠቃላይ በዞኑ በ26 ቀበሌዎች ድርቅ መከሰቱንና ከ180ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለእርዳታ መዳረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ የእንስሳትና የሰው ህይወት መጥፋቱንም ተናግረዋል፡፡
“በሳህላ ሰይምት፣ በአበርገሌ ወረዳና ዝቋላ ወረዳ ድርቅ መከሰቱንና 4ሺህ 62 እንስሳትና 6 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፣ አሁን እረዳታ በተሸለ ሁኔታ እየቀረበ ቢሆንም በቂ ግን አይደለም፡፡”
ኃላፊው አያይዘውም የተወሰኑ ቀበሌዎችበአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ስር በመሆናቸው የችግሩን መጠን ማወቅ እንደማይቻልም ተናግረዋል፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን ምግብ ዋስትና ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ሰላምይሁን ሙላት ድርቁ 35 ሄክታር የእርሻ ማሳ ያለ ጥቅም ማውሉንና 450 ሺህ ወገኖችን ለችግር ዳርጓል ብለዋል፣ ከድርቁ ድርቁን ተከትሉ በተከሸተ በሽታ የ32 ሰዎች ህይወት ማለፉንም አብራርተዋል፡፡የትምህርት ማቋረጥ ስጋት በዋግኽምራ
እስካሁን በሰሜን ጎንደር ከፌደራሉና ከክልሉ መንግስትወደ 26 ሺህ ኩንታል የእርዳታ እህል በጣም በምግብ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች መከፋፈሉን የተናገሩት የዞኑ ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ አሁንም ተከታታይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡
የዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላወቸው 20 ከመቶ ለሚሆኑ ችግረኞች የገንዘብና የእህል እርዳታ ቢደረግም ድጋፉ አሁንም ሊቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ኢትዮጵያ