ሕዳር 10/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ለንደን የሚያደርገውን የበረራ መዳረሻ ወደ ሁለት ማሳደጉን አስታወቀ።
በዚህም አየር መንገዱ ቀደም ሲል መዳረሻ ከነበረው የለንደኑ ሂትሮ አየር ማረፊያ በተጨማሪ ወደ ጋትዊክ አየር ማረፊያ በረራ እንደሚጀምር በዛሬው እለት አስታውቋል።
ይህም በእንግሊዝ የማረፊያ ብዛቱን ወደ ሶስት ከፍ እንደሚያደርገው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ብዛት ቁጥር ደግሞ ወደ 136 እንደሚያሳድገው ተገልጿል።
በመርኃ ግብሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ፣ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልሽ እና የአየር መንገዱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በሄኖክ ሃይሉ